“የአመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ” ተብሎ ተሸለመ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ታዋቂው ኢትዮጵያዊ የሶሻል ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ አቤል ብርሃኑ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ጎልደን አዋርድስ (Africa Golden Awards 2026) የ”አመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ” ሽልማት አሸናፊ ሆኗል። አቤል ሽልማቱን የተቀበለው ትላንት ምሽት በተካሄደው ደማቅ ስነ-ስርዓት ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ነው።

​አቤል ብርሃኑ ሽልማቱን ካገኘ በኋላ ባስተላለፈው መልዕክት፣ ስኬቱ ከልጅነት ህልም የተነሳና በፈጣሪ እርዳታ እውን የሆነ መሆኑን ገልጿል። “በአሮጌ ስልክ ካሜራ ስነሳ አለምን የማየት እና ታሪኮችን የማካፈል ህልም ብቻ ነበር የነበረኝ” ያለው አቤል፣ አህጉራዊ እውቅና በማግኘቱ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ገልጿል።

​የሽልማት ድርጅቱ አቤልን ለዚህ ክብር የመረጠው በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመዘዋወር የሚያቀርባቸውን የጉዞ ታሪኮችና ለአህጉሪቱ ቱሪዝም እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ ታውቋል። አቤል ብርሃኑ ለዚህ ስኬት እንዲበቃ ከጀርባው ሆነው ለደገፉት ወገኖቹ በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

​ይህ ሽልማት በኢትዮጵያ ዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ይጠበቃል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1