ዳሸን ባንክ ሸሪክ ከደንበኞቹ በአደራ የሰበሰበውን ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች አበረከተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ዳሸን ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፉ በሆነው ሸሪክ አማካኝነት ከደንበኞቹ በአደራ መልክ የሰበሰበውን 16.9 ሚሊዮን ብር ለሀገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ አድርጓል።

ስምንተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው ሸሪክ ይህንን የገንዘብ ድጋፍ ያስረከበው የባንኩን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የዳሸን ኤክስፖ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ ነው።

በዕለቱ ማብራሪያ የሰጡት የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ አምዱ ሰማን ሸሪክ ለደረሰበት ስኬት የደንበኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ባንኩ ጠንካራ የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ በማቋቋም የማህበረሰቡን እሴቶች የጠበቁ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝና ማህበራዊ ኃላፊነቱንም እየተወጣ መሆኑን አስረድተዋል።

ሸሪክ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት የቻለ ሲሆን የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑንም ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል።

የባንኩ ቺፍ ባኪንግ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን በበኩላቸው ሸሪክ በስምንት ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበው ዕድገት አስደናቂ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ ጠንካራው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ሰጭ በሚል ዓለም አቀፍ ሽልማት መቀበሉንና በአሁኑ ወቅት ከ90 በላይ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎች እንዳሉት ተገልጿል።

ዳሸን ባንክ ዓለም አቀፍ የኢስላሚክ ፋይናንስ መስፈርቶችን የሚያወጣው ተቋም (AAOIFI) ቋሚ አባል የሆነ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋም መሆኑም ተጠቅሷል።

#dashenbank #sharik #interestfreebanking #charity #ethiopianfinance #socialresponsibility #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: