በአርባ ምንጭ ከተማ የምርጫ ማስታወቂያን የቀደደው ተከሳሽ በቀላል እስራት ተቀጣ ።

- Advertisement -
Sidebar AD

የሼቻ ክፍለ ከተማ ታክቲክ ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ተወካይ ም/ኢ/ር ቤዛ ቤርገሳ እንደገለፁት ተከሳሽ ተመስገን ካርታ አይሳ ዕድሜ 25 የሆነ ዕለቱ ማክሰኞ በቀን 20/08/2018 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 12:30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ ሼቻ ክ/ከተማ ጫሞ ቀበሌ ልዩ ባይራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ7ኛ ሀገራዊ ምርጫ በአርባ ምንጭ ምርጫ ክልል የብልፅግና ፖርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የምርጫ ምልክት የሆነው የስንዴ ነዶ ያለበትን ፖስተር ወይም የምርጫ ማስታወቂያ ለህዘብ ለማስታወቅ መብራት ፖል ላይ የተለጠፈውን ሁለት ፖስተር ከፖሉ ላይ የቀደደ በመሆኑ በፈፀመው የምርጫ ማስታወቂያ በማጥፋቱ ተከሶ ፖሊስ ምርመራውን በሰው ማሰረጃ በማጣራት ለዐ/ህግ ልኳል።

ዐቃቤ ህግም በቀረበው መዝግብ ላይ የኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/201 አንቀጽ 158 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ክስ በመመሰረት ለአ/ምንጭ ከተማ መጀመሪያ ደ/ፍ/ቤት ስይቀርብ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን በማከራከር በቀን 26/08/2018 ዓ/ም በዋለው በወንጀል ችሎት ወንጀል ፈፃሚውን ያርማል ሌላውን እንደዚህ ዓይነት እኩይ ተግባራትን የሚፈፅሙትን ያስጠነቅቃል በማለት (9) ዘጠኝ ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል ።

አርባምንጭ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ህ/ግ/ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን።


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1