ኢትዮጵያ ቱርክን አሸነፈች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በአዋሽ-ወልዲያ የባቡር መስመር ግንባታ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው ከፍተኛ የሕግ ክርክር በኢትዮጵያ ድል ተጠናቋል። የቱርኩ ኩባንያ ያፒ መርከዚ (Yapı Merkezi) በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ላይ አቅርቦት የነበረው የ979.9 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ክስ በለንደን ዓለም አቀፍ የግልግል ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጓል።

​ይህ ውሳኔ ለኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት ሲሆን፣ የውሳኔው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦

​ፍርድ ቤቱ ኩባንያው ከጠየቀው ግዙፍ ክፍያ ውስጥ 750 ሚሊዮን ዶላሩን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል።

​ኩባንያው ቀደም ሲል በቅድሚያ ተከፍሎት የነበረውን 29.1 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እንዲመልስ ተወስኗል።

​ለፕሮጀክቱ ግንባታ ወደ አገር ውስጥ የገቡ ማንኛቸውም ማሽነሪዎች፣ ተሽከርካሪዎች እና የግንባታ መሣሪያዎች በሙሉ ለኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እንዲተላለፉ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

​ሪፖርተር እንደዘገበው ከሆነ፣ ይህ ውጤት አገሪቱን ሊገጥማት ከነበረው ግዙፍ የገንዘብ ኪሳራ የታደገ ከመሆኑም በላይ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ያስከበረ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ቅ​ዳሜ_ገበያ #ኢትዮጵያ #ምድርባቡር #ያፒመርከዚ #የህግድል #አዋሽወልዲያ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1