የክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ነገ ይመረቃል
#Ethiopia | ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው ንጉሥ ተብሎ ለሚጠራው ለክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ የሚሆን ግርማ ሞገስ ያለው ሐውልት ተሠርቶ መጠናቀቁ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ለታላቁ የጥበብ ሰው ያለውን አክብሮት ለመግለጽ ያስገነባው ይህ ሐውልት፣ በስድስት ኪሎ አካባቢ ወደ ምኒልክና ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ መገናኛ ላይ ቆሟል።
ነገ ማክሰኞ ጠዋት 1:00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ ስድስት ኪሎ አደባባይ (አዲስ አበባ)
የጥላሁን ገሠሠ ባለቤት ወይዘሮ ሮማንና ቤተሰቦቹ ለመላው የጥበብ ሰዎችና አድናቂዎች በቦታው እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል።
ተሳታፊዎች ተሽከርካሪዎቻቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በማቆም በምርቃቱ ላይ መታደም ይችላሉ።
የንጉሡ አሻራ
ጥላሁን ገሠሠ ስለ ሀገር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ እናትና ስለ ጀግንነት ያልዘፈነበት ርዕስ የለም። በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞና በሱዳንኛ ዜማዎቹ ህዝብን ሲያቆራኝ የኖረ ባለውለታ ነው።
ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም. በ68 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለየንም፣ ዜማዎቹ ግን ከትውልድ ትውልድ ተሻግረው ዛሬም የነፍሳችን ምግብ ናቸው።
ጥላሁን ገሠሠ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነት ራሱ ትልቅ ትርጉም የሰጠ ሰው ነው። ዛሬ ሐውልቱ ሲቆም የምናየው የሳቁንና የድምጹን ግርማ ብቻ ሳይሆን፣ ጥበብ ሀገርን እንዴት እንደምትገነባ ጭምር ነው።
ነገ ስድስት ኪሎ ላይ ሁላችንም ተገኝተን ለዚህ የሀገር ባለውለታ የሚገባውን ክብር ልንሰጥ ይገባል!
ጥላሁን ገሠሠ—የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉሥ ለዘላለም ይኖራል!
#getu #TilahunGessesse #EthiopianMusic #Legend #Monument #AddisAbaba #History #Art #KingOfMusic #ጥላሁንገሠሠ #የሙዚቃንጉሥ #ሐውልት #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.