#FastMereja I ድምጻዊ ኪቺኒ ታዋቂው ራፐር ልጅ ሚካኤል የቦክስ ስፖርት አፍቃሪ መሆኑን በመጥቀስ፣ በወራት ጊዜ ውስጥ ፊት ለፊት ተገናኝተው የቦክስ ግጥሚያ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በይፋ ገልጿል። ድምጻዊው ይህንን ፍላጎቱን ያስታወቀው የራፐሩን ስፖርታዊ ዝንባሌ መነሻ በማድረግ ሲሆን፣ ጥሪው በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ መነጋጋሪያ ሆኗል።
ልጅ ሚካኤል ለቦክስ ስፖርት ያለው ፍቅርና ክህሎት ከፍተኛ እንደሆነ እንደሚረዳ ጠቁሞ፣ ይህንን ችሎታውን በመድረክ ሳይሆን በRing ውስጥ ሊፈትነው እንደሚፈልግ በልበ ሙሉነት ተናግሯል።
ራፐር ልጅ ሚካኤል ከድምጻዊ ኪቺኒ ለቀረበለት የ”መግጠም” ጥሪ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።
Source: FastMereja









No comments yet.