በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ስም በተፈጸመ ማጭበርበር የተጠረጠሩ ታዋቂ ግለሰቦች የዋስትና መብት ተፈቀደ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በፊንቴክ የኢንቨስትመንት ስራ ላይ ተሰማርተናል በሚል በተፈጸመ የማጭበርበር ድርጊት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ አርቲስቶችና የቲክቶክ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ በዋስትና ለመፈታት የሚያስይዙትን የገንዘብ መጠን ለመወሰን ለሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የሰጠው ዓቃቢ ህግ ከአምስተኛ ተከሳሽ መንሱር ጀማል ውጪ ያሉት ሌሎች ተጠርጣሪዎች በዋስትና ቢወጡ ተቃውሞ እንደሌለው ገልጿል።

ሆኖም ፍርድ ቤቱ ዓቃቢ ህግ በመንሱር ጀማል የዋስትና መብት ላይ ያለውን ተቃውሞ በዝርዝር በጽሁፍ አዘጋጅቶ ለግንቦት ሦስት እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

#fintech #courtcase #legalnews #justice
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: