በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾች የታደሙበት በሀገራችን የመጀመሪያው ታላቅ የሰርግ ድግስ ተከናወነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቻናል ዋን ቴሌቪዥን ሙሉ ወጪያቸው የተሸፈነላቸው ሦስት ሙሽሮች ደመቅ ያለ የሰርግ ስነስርዓት አድርገዋል፡፡

ይህ በይዘቱ ለየት ያለ ፕሮግራም ሙሽሮቹን ምንም ዓይነት ወጪ ሳያስወጣቸው በነፃ የተከናወነ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የከተማዋ ስመ ጥር የዲዛይን ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ድምፃውያን፣ ዲጄዎች፣ ምርጥ ሼፎች፣ የኬተሪንግ አገልግሎት ሰጪዎች፣ የሜካፕና የፎቶ ባለሙያዎች እንዲሁም የሊሞዚን መኪና አቅራቢዎች ተሳትፈውበታል፡፡

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በቻናል ዋን ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት የታደሙበት ይህ የፍቅር ታሪክ መጀመሪያ የሆነው ልዩ የሰርግ ዝግጅት፣ በቀጣይ እሁድ ከቀኑ 6:00 ሰዓት ጀምሮ እሁድን 1 በተሰኘው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ለተመልካቾች ይቀርባል ተብሏል፡፡

ቻናል ዋን ለሙሽሮች በሰጠው ትኩረትና በፈጠረው አዲስ አቀራረብ አድናቆትን እያገኘ ይገኛል፡፡

#ቻናልዋን #ሰርግ #ፍቅር #ቴሌቪዥን #ኢትዮጵያ #ሙሽሮች #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2