ከኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን የገዙ ባለድርሻዎች ስለአክሲዮናቸው ምንም ዓይነት መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናገሩ
ኢትዮ ቴሌኮም አሥር በመቶ ድርሻውን ለኢትዮጵያውያን በሽያጭ አቅርቦ አክሲዮን ከገዙ አንድ ዓመት ከግማሽ ቢሆንም፣ የድርሻው ገዥዎች እስካሁን የትርፍ ክፍፍልም ሆነ ሪፖርት፣ በሚመለከት ምንም ዓይነት መረጃ ደርሷቸው እንደማያውቅ ገለጹ፡፡
አክሲዮኑ ለሽያጭ መቅረቡ ይፋ እንደተደረገ መግዛታቸውን ለሪፖርተር የገለጹት አቶ ኃይሉ ታደሰ የተባሉ ባለድርሻ ፣ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ለሚሆን ጊዜ መጠበቃቸውን፣ ነገር ግን እስካሁን ‹‹እየሠራን ነው ጠብቁ›› ከሚል ምላሽ ውጪ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በግልጽ እንዳልተነገራቸው ተናግረዋል፡፡
‹‹አክሲዮኑን የገዛነው ትርፋማ ሆነን ራሳችንን እንጠቅማለን በሚል ነበር፤›› የሚሉት አቶ ኃይሉ፣ ይህ እንኳን ባይሆን ቶሎ ምላሽ መሰጠት እንደነበረበትና ሥራው ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለባለአክሲዮኖቹ በግልጽ ሊነገር ይገባል ብለዋል፡፡
ኩባንያው አክሲዮኑን ለሽያጭ ካቀረበ በኋላ ምክንያት ብሎ ያቀርብ የነበረው ባለአክሲዮኖች የዲጂታል መታወቂያ ባለማቅረባቸው ስለነበር፣ ዲጂታል መታወቂያቸውን በቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት መላካቸውን ገልጸው፣ አሁንም ችግሩ ይህ ከሆነ ዲጂታል መታወቂያቸውን ለላኩና መሥፈርቱን ላሟሉ ገዥዎች የትርፍ ክፍፍልም ሆነ ሪፖርት መላክ እንዳለበት፣ ካልሆነም ምክንያቱን በግልጽ ማሳወቅ እንደሚገባው አስረድተዋል፡፡
Via_ሪፖርተር
@seledadotio

No comments yet.