የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት እና ምልጃዋ አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

እርሷ ምስራቅ ነች ልጇም የጽድቅ ጸሐይ ነው

በ325 ዓ.ም በጉባኤ ኒቂያ በነበረው የሲኖዶስ ውይይት ላይ በአደባባይ ተከራክረው ከሐዲያንን ካሳፈሩ 318 ሊቃውንት አንዱ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ነበረ።

የጌታችንን የመድኅኒታችንን መለኮታዊ ባህርይ ለሚጠራጠሩ አርዮሳውያንና በተዋሕዶ ሰው ሆኖ መክበሩን ለሚክዱ ቅዱስ ኤጲፋኒዮስ ስለ ተዋሕዶ ምሥጢርና ቅድስት ድንግል ማርያም የመለኮት እናት ስለመሆኗ ሲያስተምር “ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውና አምላክ በተዋሕዶ የከበረ ነው፡፡ በአምላክነቱ መለኮታዊ ባሕርይ ቢኖረውም እንደ ሰውነቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር ተፀንሶ በድንግልና ተወልዷል። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ 7፣14 እንደጻፈው “እግዚአብሔር ምልክት ይሰጠናል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፡፡ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ እርሱም ድንቅ መካር ኃያል የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።” በመሆኑም እመቤታችን የአምላክ እናት የእግዚአብሔር እናት ትባላለች ።

ቅዱስ ዮሐንስም በዘመኑ ለተነሱት ከሃዲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና እውነታውን አስረግጦ አስተምሮአል። የክህደት ትምህርት የሚያስተምሩትም በማቴ1÷25 “ዮሴፍም የበኩር ልጇን እስከ ምትወልድ አላወቃትም” ተብሎ ስለተጻፈ ድንግል ማርያም ጌታን ከወለደች በኋላ ከዮሴፍ ጋር በትዳር ኖራለች ብለው ለተነሱበት የተሳሳተ ሃሳብ ሲመልስ፣ እስከ የሚለው ሃረግ ወይም ቃል “ዮሴፍ የበኩር ልጇን እስከምትወልድ አላወቃትም ማለት አንድም ወንድ እንደማታውቅ አንድም እስከ የሚለው ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው፡፡ በመሆኑም ጌታን እስከምትወልድ የምትወልደው መድኃኔዓለምን እንደሆነ አላወቀም፡፡ የድኅነት ምክንያት ሆና እንደተመረጠች አያውቅም ነበር፡፡

በሉቃስ ወንጌል ላይም ማርያም ነገርን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ስለነበር ከቅዱሳን የከበረች ከመላዕክትም የበለጠች እንደነበር አያውቅም ነበር። በሌላው ጌታን በፀነሰች ጊዜ ገጽዋ ይለዋወጥ ነበር ይህንንም ሲያይ ዮሴፍ ጻድቅም ስለነበር ሳይገልጣት ተዋት። አበው እንዳስተማሩን እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ በተዋሕዶ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣልና። ድንግል ማርያም ጌታን ከመፅነሷ በፊት በፀነሰች ጊዜ ከፀነሰችም በኋላ ድንግል ናት። እንዲሁም ከመውለዷ በፊት በወለደችም ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት። ይህንንም እግዚአብሔር ስለገለጸለት ከአበይት ነቢያት መካከል አንዱ ቅዱስ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 44÷1-4 “ወደ ምስራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ ይህ በርም ዝግ ነበር፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ለዘላለም ዝግ ሆኖ ይኖራል።” አለኝ ይላል፡፡

ምስራቅ ያላት ድንግል ማርያምን ነው ፀሐይ ከምስራቅ እንዲወጣ ጨለማውንም ዓለም ብርሃን እንዲያደርግ፤ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስም ከአማናዊት ምስራቅ ከድንግል ማርያም ተልወዶ በኅጢያት ለጨለመው ዓለም የጽድቅ ብርሃን ሆኖ ተገልጧልና፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም በመኃልዬ መኃልይ 4÷12 “እህቴ ሙሽራዬ ሆይ የተዘጋ ገነት የታተመ ፈሳሽ ነሽ” በማለት ስለዘላለማዊ ድንግልናዋ ጽፏል። በቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ 4÷4 እንደጻፈው የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ያለ ዘርአ ብእሲ ወይም ያለ ወንድ ዘር ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአምላክ እናት የተወለደውን አንድያ ልጁን ላከልን፣ እርሱም የእኛን ባህርይም ባህርይ አድርጎ ተወለደ። ልጆችም ስለሆንን እግዚአብሔር አባ አባት ብለን የምንጠራበት የልጅነት መንፈስ ሰጠን፡፡ እመቤታችንም በሕቱም ድንግልና ይህን ጌታ ወለደችልን፡፡ ገዳማውያንም ይህችን እናት ዘወትር አማልጅን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1