#FastMereja I በሴት ላይ ጥቃት በማድረስ የተከሰሰው ድምፃዊ አህመድ ማንጁስ በ300 ብር ቅጣት ተቀጣ።
የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት፣ በድምፃዊ አህመድ ሁሴን (ማንጁስ) ላይ የ300 ብር የገንዘብ ቅጣት አስተላለፈ። ድምፃዊው የተቀጣው የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ መድሃኒት ይልማ በተባለች ግለሰብ ላይ አካላዊ ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ነው።
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ከመስጠቱ በፊት የአቃቤ ህግን “ጥቃቱ በሴት ላይ እና በምሽት ተፈጽሟል” የሚል የቅጣት ማክበጃ የቀረበለት ቢሆንም፣ የተከሳሹን የቅጣት ማቅለያዎች ተመልክቷል። ድምፃዊው ቀደም ሲል የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን፣ ጥፋቱን አምኖ መጸጸቱን እና የሁለት ልጆች አባት መሆኑን በመጥቀስ ቅጣት እንዲቀልለት ያቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል።
በዚህም መሰረት ችሎቱ የእስር ቅጣቱን ወደ 300 ብር የገንዘብ ቅጣት የቀየረው ሲሆን፣ ተከሳሹ የተበየነበትን ገንዘብ እንደከፈለ የዋስትናው ተመላሽ ተደርጎለት ከእስር እንዲፈታ ታዟል። ዘገባው የኢትዮጲካሊንክ ነው።
Source: FastMereja








No comments yet.