”ድምፃዊ ዮሳን ጌታሁን በሊሙዚንና በሰረገላ የታጀበ የክብር አቀባበል ሊደረግለት ነው”

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja በኦሮምኛ ሙዚቃ ስራዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ዮሳን ጌታሁን፣ ከአድናቂዎቹ ጋር በአካል የሚገናኝበት እና ልዩ የክብር እውቅና የሚሰጥበት መድረክ መዘጋጀቱ ተገለፀ።

“Ethiopian Celebrity’s Meet & Greet” የተሰኘዉ ይህ መርሀ-ግብር አዘጋጁ Tawaki Event Crew በዛሬዉ እለት በአምባሳደር ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ዝግጅቱ ድምፃዊው ለኪነ-ጥበቡ እያበረከተ ላለው አዲስ መንፈስ እውቅና ለመስጠት የታለመ መሆኑ ተገልጿል።

በዕለቱ ድምፃዊ ዮሳን ጌታሁን ወደ ዝግጅቱ ስፍራ የሚገባው በሊሙዚን እና በፈረስ ሰረገላ ታጅቦ በሚደረግ ደመቅ ያለ የክብር አቀባበል እንደሆነ የአዘጋጅ ድርጅቱ ተወካዮች አቶ መሀመድ እና አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የቀይ ምንጣፍ (Red Carpet) አቀባበል፣ የፎቶ ፕሮግራም፣ አድናቂዎች ለድምፃዊው ጥያቄ የሚያቀርቡበት የውይይት መድረክ፣ የእራት ግብዣ እና የክብር ካባ የማልበስ ስነ-ስርዓት እንደሚከናወን ተገልጿል።

አዘጋጆቹ በመግለጫቸው ላይ እንደተናገሩት፣ “የታዋቂዎችን ስራ ማክበር ባህላችን ሊሆን ይገባል” በሚል እምነት ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ለተዋናይት ሰላም ተስፋዬ በሸራተን አዲስ፣ እንዲሁም ለዓለም አቀፉ የጃዝ ሙዚቃ ፈር ቀዳጅ ለዶክተር ሙላቱ አስታጥቄ በጊዮን ሆቴል መሰል የክብር መድረኮችን ማዘጋጀቱ አንስተዋል።

ድምፃዊ ዮሳን ጌታሁን በተለይም “ቡሎ” እና “ባለጊዜ“ በተሰኙ ስራዎቹ በማህበራዊ ሚዲያ እና በአድናቂዎች ዘንድ ያለው ከፍተኛ ተቀባይነት ለዚህ የክብር መድረክ ተመራጭ እንዳደረገው ተጠቁሟል።

እንዲሁም ይህ መድረክ ከክብር እና ምስጋናው ባሻገር፣ አርቲስቱ የህይወት ልምዱን ለወጣቶች የሚያካፍልበት ሙያዊ መድረክ እንደሚሆንም ታውቋል።

ከ2016 ጀምሮ በ(Event Planning) ዘርፍ በንቃት እየሰራ የሚገኘው ታዋቂ ኢቨንት ፣ ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች፣ የፋሽን ትርኢቶች እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ ከመንግስትና ከግል ተቋማት ጋር በጋራ ሰርቷል።





Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: