ልዩ መረጃ!
‹‹ተዘጋጅተናል..›› ጀነራል አበባው ታደሰ በጦር ግንባር ታዩ!
የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ በሰሜን ምእራብ ዕዝ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑ ታውቋል፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሓኑ ጁላ የላኩትን መልዕክትም ለሰራዊቱ ማድረሳቸውን አንዳፍታ ሚዲያ ከሰራዊቱ ድህረገጽ ተመልክቷል፡፡
በፌዴራል መንግስቱ እና በሕውሓት ኃይሎች መካከል ያለው ውጥረት ባየለበት በዚህን ወቅት፤ ጀነራሉ የሰራዊቱን የግዳጅ ዝግጁነት ለመመልከት በሰሜን ምእራብ ዕዝ ተገኝተዋል፡፡ ጀነራሉ በግንባር የሚገኙ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የጦር ክፍሎችን ወታደራዊ ፣አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ዝግጁነት ተዘዋውረው ተመልክተዋል የተባለ ሲሆን፤ እንዲህ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡- ‹‹ዕዙ ከታሪካዊ ጠላቶቻችንም ይሁን ከባንዳዎች ሊሰነዘር የሚችል ጥቃትን መመከትና መደምሰስ በሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል›› የሚል። ጀነራል አበባው ‹ባንዳ› ሲሉ የጠሯቸውን አካላት በስም ባይጠሩም፤ ከዚህ ቀደም በመከላከያ አመራሮች ‹ባንዳ› በሚል የሚጠራው በአካባቢው ያለው ኃይል ግን የፋኖ አማጺ ቡድን እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ቀጥለውም ‹‹የህወሃትን አገር የማፍረስ ተከታታይ ወረራ በመመከትና ሀገርን በማፅናት ትልቅ ሚና የነበረው ጠንካራ ዕዝ›› በማለት አሞካሽተውታል፡፡ ‹‹ሰሜን ምዕራብ ዕዝ በአማራ ክልል ግጭትና ሁከት ለመፍጠር በተንቀሳቀሰው የሀገር ውስጥ ባንዳ በሆነው ፅንፈኛው ቡድን ላይ ጠንካራ ምት በማሳረፍ ያሰበውን ኢትዮጵያን የማጥፋት ሴራ በማክሸፍ ፅንፈኛው ቅስሙ እንዲሰበር እና እጅ እንዲሰጥ በማድረግ ወገን የኮራበት፤ ጠላት ያፈረበትን ከፍተኛ ስራ የሰራ ዕዝ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡
@seledadotio

No comments yet.