በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2018 በጀት አመት አንድ ሚሊዮን ኮንዶም ለማሰራጨት ቢታቀድም ባለፋት ስድስት ወራት 7 መቶ ሺህ ኮ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2018 በጀት አመት አንድ ሚሊዮን ኮንዶም ለማሰራጨት ቢታቀድም ባለፋት ስድስት ወራት 7 መቶ ሺህ ኮንዶም ብቻ መሰራጨቱ ተገለፀ።
በአሁኑ ወቅት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤች አይቪ ኤድስን ለመከላከል በተደረገው ጥረት የበሽታው ስርጭት የመቀነስ አዝማሚያ ማሳየቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
በቢሮው የኤችአይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ወዲ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ምንም እንኳን በክልሉ የበሽታው ስርጭት አድማስ የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች ላይ መዘናጋቶች ይታያሉ።
በሽታውን ለመከላከል ከሚረዱ ነገሮች መካከል አንዱ የሆነው ኮንዶም እንደመሆኑ ስለ ኮንዶም አጠቃቀም እየተሰራ ካለው የግንዛቤ ስራ ውጪ ለማህበረሰቡ እንዲሰራጭ ተደርጓል ብለዋል።በክልሉ ከሁለት አመት በፊት የነበረው የኮንዶም እጥረት አሁን ላይ መቀረፋን የገለፁት አቶ ታረቀኝ ባለፋት ስድስት ወራት 7መቶ ሺህ ኮንዶም እንዲሰራጭ መደረጉን አስረድተዋል።
እስከ በጀት አመቱ ማብቂያ ድረስ አንድ ሚሊዮን ኮንዶምን ለማህበረሰቡ ለማሰራጨት እቅድ መያዙን አስታውሰው በአፈፃፀሙ መሰረት የእቅዱን 62 በመቶ ብቻ ማከናወን ተችሏል ሲሉ ዳይሬክተሩ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።ይህም ተደራሽ ማድረግ ያልተቻለባቸው አካባቢዎች እንዳሉ የሚያሳይ ነው ያሉ ሲሆን በታቀደው ልክ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
በቅድስት ደጀኔ
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1