የህዝብ ንቁ ተሳትፎ የ20 ሚሊዮን ብር የኬብል ስርቆትን አከሸፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ስፖርት ፌደሬሽን አካዳሚ ፊት ለፊት ለኮሪደር ልማት የተዘጋጀ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ንብረት ለመስረቅ የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ግለሰቦቹ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን 9 ጥቅል የኤሌክትሪክ ኬብሎች በክሬን በመታገዝ ሲጭኑ እጅ ከፍንጅ የተያዙት ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ረፋድ ላይ ነው።

ለስርቆቱ የኮድ 3-47749 ኢት የሰሌዳ ቁጥር ያለው የክሬን ተሽከርካሪ የተጠቀሙት ተጠርጣሪዎቹ አስመራ ነገራ (አሽከርካሪ)፣ ኤልያስ በርሄ (ረዳት) እና ወርቁ ኖራህ (ተባባሪ) ንብረቱን እንድናመጣ ታዝዘን ነው የሚል የሀሰት ምክንያት ቢያቀርቡም በአካባቢው የነበረው ማህበረሰብ በሰጠው ጥቆማ ሊያዙ ችለዋል።

ፖሊስ ባደረገው ማጣራት ተጠርጣሪዎቹ በኮሪደር ልማት ስራው ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የህብረተሰቡ ፈጣን መረጃ ለወንጀለኞቹ መያዝ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጾ ይህም በፖሊስና በህዝብ መካከል ያለውን ጥብቅ ግንኙነት የሚያሳይ መሆኑን አመልክቷል።

መሰል የልማት ስራዎችንና የሀገር ሀብቶችን ከጥፋት ለመታደግ ህዝቡ እያደረገ ያለው ክትትል ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ቀርቧል።

#ዜና #አዲስአበባ #የወንጀልመከላከል #የኮሪደርልማት #ፖሊስ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: