በከባድ የሙስና ወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦች ይፋ ተደረጉ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በከባድ የሙስና ወንጀል የሚፈለጉ አራት ግለሰቦችን ማንነትና ምስል ዛሬ ይፋ አደረገ። ፖሊስ እነዚህ ግለሰቦች በፈጸሙት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ምክንያት በህግ ጥላ ስር ውለው ምርመራ እንዲደረግባቸው የህዝብ ትብብር መጠየቁን አስታውቋል።

​በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የሚፈለጉት ግለሰቦች፦

​በረከት ወርቁ አደራ

​ጌታቸው አምሻ ያየሁ

​ይልቃል የኔሰው ዘለቀ እና

​አቡሽ አየለ ገነት ናቸው።

​እነዚህ ግለሰቦች በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በህግ የሚፈለጉ በመሆናቸው፣ ህብረተሰቡ ግለሰቦቹን በሚመለከት ማንኛውንም መረጃ ካለው ለፖሊስ እንዲያሳውቅ ጥሪ ቀርቧል። መረጃ ያላቸው ዜጎች በስልክ ቁጥር 0111119475 ደውለው እንዲጠቁሙ ፖሊስ አሳስቧል።

​የፌደራል ፖሊስ ለወንጀል መከላከልና ለህግ የበላይነት መከበር የህዝቡ የተለመደ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልጾ፣ ጥቆማ የሚሰጡ አካላት ምስጢራዊነታቸው እንደሚጠበቅም በመረጃው አመልክቷል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: