#Ethiopia | በቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ አ.ማ፣ በቴክኖሎጂው ዘርፍ እያከናወነ ባለው ስራ ለሀገራዊ ፕሮጀክቶችና ለሰብአዊ ድጋፎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገለጸ።
ቻፓ የክፍያ መተግበሪያውን በመጠቀም ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉትን የሚያካትት ሲሆን በብሔራዊ መታወቂያ ዘርፍ ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ባሉበት ሆነው ክፍያ በመፈጸም የብሔራዊ መታወቂያ ስርጭት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል ፤ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ “MyGerd” የተሰኘ የበይነ መረብ የክፍያ ፕላትፎርም በማበልጸግ፣ ከዲያስፖራው ማህበረሰብ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ያለ ምንም ኮሚሽን በድምሩ 1,270,035,973 (አንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሚሊዮን ሰላሳ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሶስት) ብር ገቢ እንዲሰበሰብ አድርጓል።
ኩባንያው “From Shared Success to Future National Missions” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የቻፓ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ናይል ኃይለማርያም እንደገለጹት፤ ቻፓ መንግስት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ጥሪ ባደረገበት ወቅት ቴክኖሎጂውን በሶስት ቀናት ውስጥ በማበልጸግ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ከግድቡ በተጨማሪ፣ በተለያዩ ምክንያቶች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚውል በሚሊዮን የሚቆጠር የአሜሪካ ዶላር ከዲያስፖራው እንዲሰበሰብ በማድረግ ረገድ ኩባንያው የላቀ ሚና ተጫውቷል።
አቶ ናይል አክለውም ቻፓ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር የአገልግሎት ተደራሽነቱን እያስፋፋ ይገኛል ፤ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይም ጉልህ ተሳትፎ ማድረጋችንን እንቀጥላለን ብለዋል።
በዛሬው እለት በተካሄደው የ“Gratitude Gathering” ዝግጅት ላይ፣ ቻፓ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ እና ለሰብአዊ ድጋፎች ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክብር ሽልማት ተሰጥቶታል። ቻፓ በአሁኑ ወቅት ለመንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu



Source: GetuTemesgen








No comments yet.