#Ethiopia | በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኢራን የባህር ኃይል እና በአሜሪካ የጦር መርከቦች መካከል የትጥቅ ግጭት መከሰቱን የኢራኑ ፋርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
ትናንት ምሽት አሜሪካ በአንድ የኢራን የንግድ መርከብ ላይ በሰነዘረችው ጥቃት ሳቢያ በመርከቧ ላይ ከፍተኛ እሳት የተነሳ ሲሆን፣ በሰው ሕይወትና አካል ላይም ጉዳት ደርሷል።
በጥቃቱ ሳቢያ በመርከቧ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ላይ የደረሰው ጉዳት እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
- 10 መርከበኞች የተለያዩ የመቁሰል አደጋዎች ደርሶባቸዋል።
- መጀመሪያ ላይ 5 መርከበኞች የጠፉ ቢሆንም፣ የሚናብ ካውንቲ ገዥ መሐመድ ራድመህር እንደገለጹት ከሆነ የኦንዱ መርከበኛ አስከሬን ተገኝቷል።
-አሁንም ደብዛቸው ያልታወቁ ቀሪ 4 መርከበኞችን ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
ይህ በዓለም አቀፍ የንግድና የነዳጅ ዝውውር ቁልፍ በሆነው የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ የተከሰተው ግጭት፣ በቀጠናው ያለውን ወታደራዊ ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ተሰግቷል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ቅዳሜ_ገበያ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.