#Ethiopia | በአፍሪካ ግዙፉ የጠለፋ ዋስትና ሰጪ ተቋም የሆነው ”አፍሪካ ሪ” ፣ የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል እና 180ኛ መደበኛ የቦርድ ስብሰባውን በአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ አካሂዷል።
እ.ኤ.አ በየካቲት 24 ቀን 1976 በያውንዴ ካሜሩን በአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) አባል በነበሩ 36 ሀገራት ጥረት የተመሠረተው ይህ ተቋም፣ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ለአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገትና ለኢንሹራንስ ዘርፉ መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል።
ተቋሙ ባለፉት 50 ዓመታት ከ500 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የመልሶ መድን ሽፋን በተለያዩ ዘርፎች ሰጥቷል።
በ2025 በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን 199 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፣ አጠቃላይ ሀብቱም 2.69 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።
በአሁኑ ወቅት 42 የአፍሪካ ሀገራትን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክን እና 112 የመድን ኩባንያዎችን በአክሲዮን ባለቤትነት ይዟል።
ተቋሙ ከዓለም አቀፍ ደረጃ አሰጣጥ ተቋማት (S&P እና AM Best) የ “A” (ጠንካራ/Excellent) ደረጃን አግኝቷል።
ኢትዮጵያ በተቋሙ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላት ሲሆን፣ አፍሪካ ሪ ከ2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ የራሱን ቢሮ ከፍቶ እየሠራ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት በካሳንቺስ አካባቢ ያስገነባው አዲሱ ሕንፃ ተቋሙ በኢትዮጵያ ያለውን የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንትና ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሆኗል።
በተጨማሪም ተቋሙ ለኢትዮጵያ የመድን ኩባንያዎች የቴክኒክና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል።
ባለፈው ምሽት በስካይላይት ሆቴል በተካሄደ ደማቅ የጋላ ኮክቴል ሥነ-ሥርዓት የቦርድ አባላት፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ታድመዋል።
የአፍሪካ ሪ ዋና መሥሪያ ቤት በሌጎስ ናይጄሪያ ቢሆንም፣ በቀጣዩ ወር ሰኔ 2026 በአቡጃ አዲስ የመሥሪያ ቤት ሕንፃ እንደሚመረቅ ታውቋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu



Source: GetuTemesgen









No comments yet.