#Ethiopia | በቲክቶክ ስሙ ፕሮፌት ፊቃዱ በመባል የሚታወቀው ግለሰብ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልን እና የካውንስሉን አባል ቤተ እምነቶች ስም በመጥቀስ በጀርመን ከሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት ጋር ወንጌል አማኞችን ወደ ጀርመን ለመላክ ትምህርት ለማስተማር ስምምነት እንዳደረገ በማስመሰል የወንጌል አማኞች ተመዝግበው ወደ ጀርመን በመሄድ ትምርህት መማር እንደሚችሉ ፣ የትምህርት ወጪውም በሌሎች አካላት እንደሚሸፈን ከዛም በኋላ በአውሮፓ የአገልግሎት እድል እንደሚመቻችላቸው ሙሉ በሙሉ የሀሰት የሆነ መረጃ በማሰራጨት ላይ ይገኛል።
በመሆኑም በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው ሀሰተኛ መሆኑን አውቃችሁ ቅዱሳን ከእንደዚህ አይነት መረጃዎች ራሳቸውን እንድትጠብቁ እያሳሰብን በየትኛውም አከባቢ በእንደዚህ አይነት የሀሰት ተግባር ላይ ተሰማርተው ማህበረሰቡን እያሳሳቱ የሚገኙ አካላትን በአቅራቢያው ለሚገኙ የህግ አካላት ወይም ለካውንስሉ ህግ ክፍል በአካል በመቅረብ ጥቆማ በመስጠት እንድትተባበሩ በአክብሮት እንጠይቃለን ።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል
Source: GetuTemesgen









No comments yet.