ማንቼስተር ዩናይትድ ከሰንደርላንድ 0 – 0

- Advertisement -
Sidebar AD

ቦርንማውዝ ፉልሃምን 1 ለ 0
ብራይተን ወልቭስን 3 ለ 0

#Ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ36ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ ከሰንደርላንድ ጋር ያደረገው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ቀይ ሰይጣኖቹ ከሦስት ተከታታይ ድሎች በኋላ ነጥብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጋሩበት አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።

በሌላ በኩል ቦርንማውዝ ፉልሃምን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ ተስፋውን አድሷል።

በዚህ ጨዋታ ከሁለቱም ወገን አንደርሰን እና ክሪስት በፈጸሙት ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል።

ብራይተን በበኩሉ ወልቭስን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ ሂንሽልውድ፣ ሉዊስ ደንክ እና ያኩብ ሚንዝ የድል ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል።

ቀደም ብሎ በአንፊልድ ስታዲየም የተደረገው የሊቨርፑል እና የቼልሲ ተጠባቂ ፍልሚያ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

ለሊቨርፑል ራያን ግራቨንበርግ ግብ ሲያስቆጥር ለለንደኑ ክለብ ቼልሲ ደግሞ ኢንዞ ፈርናንዴዝ የአቻነቷን ግብ አስቆጥሯል።

ውጤቱ ቼልሲ ካጋጠሙት ተከታታይ ሽንፈቶች እንዲያገግም ሲረዳው ሊቨርፑል ግን በሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎው ላይ ጥያቄ እንዲያንዣብብ አድርጎበታል።

#PremierLeague #FootballNews #EPL #Sports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: