የካቮድ ኮሜርሻል ሪል እስቴት ግዙፍ የንግድ ማዕከላት ግንባታ እና የሽያጭ ኤክስፖ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የንግድና የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ካቮድ ኮሜርሻል ሪል እስቴት በአዲስ አበባ በተመረጡ ሶስት ስፍራዎች ላይ ግዙፍ የንግድ ማዕከላትን በመገንባት ላይ ይገኛል።

ተቋሙ በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ 17 የንግድ ማዕከላትን (ሞሎችን) ገንብቶ ለማጠናቀቅ በያዘው እቅድ መሠረት በአሁኑ ወቅት የሦስቱ ግንባታ በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።

አራተኛው ፕሮጀክት ደግሞ በመርካቶ መሀል አራት ኪሎ አካባቢ በቅርቡ በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል።

እነዚህ የንግድ ማዕከላት በሸሮሜዳ፣ በካዛንችስ፣ በመገናኛ እና በመርካቶ አካባቢዎች የሚገነቡ ሲሆን በተለይም ለንግዱ ማኅበረሰብ ምቹና ዘመናዊ የሥራ ቦታን ለመፍጠር ያለሙ ናቸው።

ግንባታዎቹ ከንግድ ቦታዎች በተጨማሪ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ የባቡር፣ የታክሲና የሜትር ታክሲ መነሻና መድረሻ ተርሚናሎችን በከርሰ ምድር ውስጥ አካተው የያዙ በመሆናቸው ለደንበኞችና ለነጋዴዎች ልዩ ምቾትን ይሰጣሉ።

ካቮድ ኮሜርሻል ሪል እስቴት እነዚህን ዘመናዊ የንግድ ቦታዎች ለተጠቃሚዎች ለማስተዋወቅ እና ለመሸጥ በጊዮን ሆቴል ከግንቦት 8 እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ልዩ የሽያጭ ኤክስፖ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።

በዚህ መርሐ ግብር ላይ የሚሳተፉ ደንበኞች እስከ 40 በመቶ የሚደርስ የዋጋ ቅናሽ የሚያገኙ ሲሆን ክፍያውንም በረጅም ጊዜ የክፍያ ሥርዓት እንዲያጠናቅቁ የሚያስችሉ ልዩ ዕድሎች ተመቻችተዋል።

በተለይም ለአገር በቀል የእጅ ጥበብ ሥራዎችና ለተለያዩ የንግድ ዘርፎች ተስማሚ የሆኑ ክፍሎች የተዘጋጁ በመሆናቸው ፍላጎት ያላቸው ነጋዴዎች በቦታው ተገኝተው የንግድ ሱቆቻቸውን እንዲመርጡ ጥሪ ቀርቧል።

#ሪልእስቴት #ንግድማዕከል #ኢንቨስትመንት #አዲስአበባ #የንግድኤግዚቢሽን #ካሽሪልእስቴት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1