#Ethiopia | የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቢኒያም ኤሮ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሚዲያ ታሪክ ውስጥ ቀዳሚ ስፍራ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የነበሩበትን ውስብስብ ችግሮች ለመቅረፍ መንግስት የዘረጋው የሪፎርም ስራ ለተገኘው ውጤት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
ተቋሙ ቀደም ባሉት ጊዜያት የመዋቅር ክፍተቶች፣ ግልጽነት የጎደለው የኤዲቶሪያል ፖሊሲ፣ የብዝሃነትና የተደራሽነት ጉድለቶች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኋላቀርነት በስፋት ይፈታተኑት እንደነበር ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታውሰዋል፡፡
ይህ የለውጥ ሂደት መፈታተን የነበሩባቸውን መሰናክሎች ደረጃ በደረጃ በመለየት ውጤታማ ስራዎች እንዲከናወኑ አስችሏል፡፡
ከተመዘገቡት ስኬቶች መካከልም በክልል ከተሞች በርካታ ስቱዲዮዎችን መገንባት፣ የዲጂታል ሚዲያ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ፣ ከዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ጋር ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንዲሁም የሀገር ውስጥ ቋንቋዎችን ቁጥር በመጨመር ተደራሽነትን ማስፋት የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
#EBC #MediaReform #Journalism #EthiopianNews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.