በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ፣ በነዳጅ የሚሰሩ 1,200 የህዝብ ማመለሻ አውቶብሶችን ሞተር፤ በኢትዮጵያ መመረት የጀመረውን የተፈጥሮ ጋዝ እንዲጠቀሙ ለመቀየር 1.4 ቢሊዮን ብር በጀት እንደሚያስፈልግ የከተማይቱ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ።
በመዲናይቱ የሚገኙ አውቶብሶችን ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተጠቃሚነት የመቀየር ሙከራ መጀመሩንም ቢሮው አስታውቋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ይህን ያስታወቁት፤ ዛሬ አርብ ሚያዝያ 30 በተካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ባካሄደው ጉባኤ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ነው።
በአሁኑ ወቅት ያለው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት እና የዋጋ ንረት የተመለከቱ ጉዳዮችን በማብራራያቸው ያነሱት አቶ ያብባል፤ ለዚህ ችግር በመፍትሔነት ከተቀመጡት ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ የሚጠቀሙ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ማበራከት እንደሆነ አስረድተዋል።
በሶማሌ ክልል በሚገኘው የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት አማካኝነት ኢትዮጵያ የጋዝ ምርት ባለቤት መሆን መጀመሯን የጠቆሙት አቶ ያብባል፤ ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ “የከተማ አውቶብሶችን ወደ ጋዝ ሞተር የመቀየር አቅጣጫ” ማስቀመጣቸውን አስታውሰዋል። በዚህ መሰረት አውቶብሶችን ወደ ጋዝ የመቀየር ሙከራ መጀመሩን ገልጸዋል።
“እንደከተማ 1,200 የሚሆኑትን፣ ቀድመው ያሉትን የከተማ የነዳጅ አውቶብሶች፣ ወደ ጋዝ ሞተር የመቀየር እንቅስቃሴ ተጀምሯል። የጋዝ ስቴሽኑን ቃሊቲ ዲፖ ገንብተን አጠናቀናል። ከዚህ በተጨማሪም ሁለት አውቶብሶች ላይ የሞተር ገጠማ ተደርጓል። ይሄም ሙከራ እየተካሄደ ነው ያለው። ይህ ሙከራ ሲጠናቀቅ 1,200 አውቶብሶችን ወደ ጋዝ የምንቀይር ይሆናል” ሲሉ የቢሮው ኃላፊ አብራርተዋል።
Via Ethiopia Insider
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.