#Ethiopia | የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ በኬንያ ናይሮቢ የሚካሄደውን የ”አፍሪካ ፎርዋርድ” (Africa Forward) ጉባኤ ካጠናቀቁ በኋላ፣ በመጪው ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለአጭር የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ እንደሚገቡ ታውቋል።
ይህ ጉብኝት ከመደበኛው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባለፈ፣ የፈረንሳይን የንግድ ጡንቻ በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ለማፈርጠም የታለመ እንደሆነ ተመልክቷል።
ፕሬዝዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ዝም ብለው ሳይሆን፣ የፈረንሳይን ግዙፍ ኩባንያዎች መሪዎች በክብር አስከትለው ነው።
የካፒታል ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ የፕሬዝዳንቱ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ነው። በተለይም በልዑካን ቡድኑ ውስጥ የተካተቱት ተቋማት የጉብኝቱን ክብደት ያሳያሉ፦
ካርፉር (Carrefour): በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቀው የችርቻሮ ንግድ ተቋም፣ ከኢትዮጵያው ሚድሮክ (MIDROC) ጋር በፈጠረው የፍራንቻይዝ ስምምነት አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት እንቅስቃሴ እየጀመረ ይገኛል።
ሜሪዲያም (Meridiam): በትላልቅ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶች ላይ የሚንቀሳቀሰው ድርጅት አመራሮችም የጉዞው አካል ናቸው።
ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የገበያ ክፍትነት፣ እንደ ፈረንሳይ ያሉ የአውሮፓ ሀገራት ቀልባቸውን ወደ አዲስ አበባ እንዲያዞሩ አድርጓቸዋል።
ማክሮን በጉብኝታቸው ወቅት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ከሚያደርጉት ውይይት ባሻገር፣ የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ የሚያስችሉ መንገዶች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ይህ ጉብኝት የፈረንሳይ “የንግድ ዲፕሎማሲ” በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ተጽዕኖ ለማሳረፍ የሚያደርገው ጥረት አካል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
የፈረንሳይ ውበት እና የኢትዮጵያ የንግድ ዕድሎች በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ቆይታ ምን አይነት ውጤት ይዘው እንደሚመጡ በጉጉት የሚጠበቅ ይሆናል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#Ethiopia #France #EmmanuelMacron #Investment #AddisAbaba #Carrefour #BusinessDiplomacy #AfricaForward
Source: GetuTemesgen









No comments yet.