ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የተጨዋች ዝውውር እገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ተጥሎበት የነበረው የተጨዋቾች ዝውውር እግድ በጊዜያዊነት ተነስቷል፡፡

ክለባችን የቅጣት መክፈያ ገንዘቡን ከአቶ ጀማል አህመድ በስጦታ ባገኘ በሁለት ቀናት ውስጥ ለአራቱ ከሳሽ ተጫዋቾች ሙሉ ክፍያ ከቅጣት ጋር ከፍሎ ቢያጠናቅቅም ሞሀመድ ላሚን ኮኔ ለፊፋ ያስገባው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ትክክል ባለመሆኑ ምክንያት ገንዘቡ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተመላሽ ተደርጓል፡፡ ተጨዋቹ እስከ አሁን ባለመላኩ ምክንያትም እገዳው ሳይነሳ ሳምንታት ቆይተዋል፡፡

ክለባችንም የተጠየቀውን ሁሉንም ህጋዊ ሁኔታዎች ማሟላቱንና የኮኔ ገንዘብም ያልተከፈለው በተጨዋቾ የራሱ ችግር መሆኑን ገልፆ ለፊፋ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ ፊፋ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጥያቄ በመቀበል ኮኔ ትክክለኛውን የባንክ ሂሳብ ቁጥሩን እንዲልክና ክለባችንም የኮኔን ክፍያ እስከሚከፍል ድረስ ተጥሎበት የነበረው እግድ በጊዜያዊነት እንዲነሳ ወስኗል፡፡ የኮኔ ክፍያ በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሲጠናቀቅ ክለባችን በቋሚነት ከእግድ ነጻ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

ክለቡ በእነዚህ አራት ተጫዋቾች ቀርቦበት የነበረውን ከፍተኛ ክፍያ በመፈጸም ክለቡን ከእገዳ ነጻ እንዲሆን ያደረጉት የክለባችን ዋነኛ ደጋፊ እና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ናቸው፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2