#Ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ደማቅ ስም ያለው ተወዳጁ ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ግማሽ ክፍለ ዘመን ያስቆጠረበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ እያከበረ ይገኛል።
ክለቡ ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት ግንቦት 1 ቀን በሳሪስ አካባቢ በሚገኙ የቡና ሰራተኞች ንጋት ኮከብ በሚል መጠሪያ መመሥረቱ የሚታወስ ነው።
በወቅቱ በመኢሰማ ስር ከነበሩ ቡድኖች አንዱ ሆኖ በሦስተኛ ዲቪዚዮን ውድድሩን የጀመረው ክለቡ በ1975 ዓም የኢትዮጵያ ቡና ገበያ የሚለውን ስም የያዘ ሲሆን ከ1988 ዓም ጀምሮ ደግሞ አሁን የሚጠራበትን ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የሚለውን ሀገራዊ ስያሜ አግኝቷል።
ክለቡ በታሪኩ በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ ሲሆን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን 2 ጊዜ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫን 6 ጊዜ ማንሳት ችሏል።
በተጨማሪም 4 ጊዜ የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን እና 1 ጊዜ የክለቦች ህብረት ዋንጫን በክብር መደርደሪያው ላይ አስቀምጧል።
ንጋት ኮከብ ተብሎ ሲመሰረት የመጀመሪያ ጨዋታውን ሳሪስ ላይ ወንድማማቾች ከተባለ ቡድን ጋር ያደረገው ክለቡ በ1990 ዓም በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ የነሐስ ሜዳሊያ በማምጣት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ክለብ መሆን ችሏል።
ኢትዮጵያ ቡና በዋናው ቡድን በወጣቶችና በሴቶች እግር ኳስ ከመሳተፉም በላይ ባለፉት 50 ዓመታት ከ5 በላይ በሚሆኑ የተለያዩ የስፖርት አይነቶች ለሀገሪቱ ብሄራዊ ቡድን በርካታ ታላላቅ ስፖርተኞችን ያፈራ አንጋፋ የክለብ መሆኑ ይታወቃል።
እንኳን አደረሳችሁ ..ቡናማዎቹ
ጋዜጠኛ ዐቢይ ዘላለም
#ethiopiancoffee #coffeesportclub #ethiopianfootball #goldenjubilee #premierleague #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen









No comments yet.