#Ethiopia | በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የሴቶችን የጤና ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመውና በ“የኔ ሄልዝ” አዘጋጅነት የቀረበው 4ኛው የጤና አውደ-ርዕይ በስኬት ተጠናቋል።
ዝግጅቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የ“የሴቶች ጤና ሳምንት” መነሻ በማድረግ፣ በሀገራችን ሴቶች ላይ የጤና ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ ልዩ መድረክ ሆኖ አልፏል።
የ“የኔ ሄልዝ” መስራችና ስራ አስኪያጅ ቅድስት ተስፋዬ እንደገለጹት፣ ዝግጅቱ ባለፉት ሶስት ዓመታት በእንጦጦ ፓርክ ሲከናወን የቆየ ሲሆን፤ ዘንድሮ ግን ለተሳታፊዎች ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ወደ መስቀል አደባባይ መምጣቱን ገልጸዋል።
ተሳታፊዎች ነፃ የጤና ህክምና እንዲያገኙ፣የተደረገ ሲሆን በሁለተናዊ የጤና አጠባበቅ ዙሪያ የምክር አገልግሎት ተሰጥቷል።
መድረኩ በ“የኔ ሄልዝ”፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና በአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የጋራ ጥረት የቀረበ ነው።
ተሳታፊዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን፣ ዳንስና የተለያዩ ጨዋታዎችን እያከናወኑ ስለ ጤናቸው ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል።
ሴቶች በቤተሰብ ውስጥ ያላቸውን መሪነት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የጤና መረጃን መቼ እና የት ማግኘት እንዳለባቸው ትምህርት ተሰጥቶበታል።
ይህ አውደ-ርዕይ የተለያዩ የጤና ተቋማት፣ የላቦራቶሪ ባለሙያዎችና የህክምና መሣሪያ አቅራቢዎች ምርታቸውንና አገልግሎታቸውን ለህዝብ ያስተዋወቁበት ትልቅ የንግድና የሙያ ትስስር መድረክም ሆኖ አገልግሏል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu



Source: GetuTemesgen








No comments yet.