በታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሣ እና በሻኩራ ፕሮዳክሽን ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የንብረት እና የባንክ ሂሳብ እገ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ካሙዙ ካሣ እና በሻኩራ ፕሮዳክሽን ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የንብረት እና የባንክ ሂሳብ እገዳ መጣሉ ተሰማ።
ይህ እርምጃ የተወሰደው “ኢትዮጵያ” በተሰኘው የባህል ማስተዋወቅ ፕሮጀክት ላይ በተሳተፉ 37 አርቲስቶች የቀረበባቸውን የ30.8 ሚሊዮን ብር ክስ ተከትሎ ሲሆን፣ አርቲስቶቹ በቻይና እና በሩሲያ ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት 11 የባህል ትርኢቶችን ቢያቀርቡም የተስማሙበት ክፍያ እና የልምምድ አበል እንዳልተከፈላቸው ገልጸዋል።
አቀናባሪ ካሙዙ ካሣ በበኩላቸው ክፍያዎችን በስምምነቱ መሠረት እየፈጸሙ መሆናቸውን በመጥቀስ ክሱን ቢያስተባብሉም፣ ፍርድ ቤቱ ግን ጉዳዩ በህግ ታይቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በአቀናባሪው ስም ያሉ ማናቸውም ንብረቶች እና በአራት ባንኮች የሚገኙ የባንክ ሂሳቦች ለ20 ቀናት ታግደው እንዲቆዩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2