ዶክተር ፀዳለ ለገሰ በዓለም አቀፍ የሥራ ፈጣሪዎች ውድድር የኢትዮጵያውያንን ድጋፍ ትሻለች
#Ethiopia | በባህር ዳር ከተማ ተወልዳ ያደገችውና በአሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖረው ፋርማሲስት ዶክተር ፀዳለ ለገሰ በፈጠራ ስራዋ በዓለም አቀፍ የሥራ ፈጣሪዎች ውድድር ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች።
ዶክተር ፀዳለ የልጇን የፀጉር ችግር ለመፍታት ባደረገችው ጥናት ያዘጋጀችው ሰዲ የተሰኘው የተፈጥሮ የፀጉር ቅባት ለውድድር ቀርቦ አምስተኛውን ዙር በብቃት በማለፍ አሁን ላይ በመጨረሻው የሩብ ፍፃሜ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ይህንን ውድድር ማሸነፏ ድርጅቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ዕውቅና እንዲያገኝ ከማድረጉም ባለፈ ታዋቂው ቢሊየነር ዴይመንድ ጆን በሚመራው የሥራ ፈጠራ መድረክ ላይ የመሳተፍ ዕድል ያስገኝላታል።
በተጨማሪም የ25 ሺህ ዶላር የገንዘብ ሽልማት የሚያሰጥ ሲሆን ዶክተር ፀዳለ ይህንን ገንዘብ የድርጅቷን ምርቶች ለማስፋፋትና ለተጨማሪ የፀጉር እንክብካቤ ግብዓቶች ልማት እንደምታውለው ገልፃለች።
የሀገራችን ተወላጅ የሆነችው ይህች ጠንካራ ሴት ውጤታማ እንድትሆንና የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ መድረክ እንድታስጠራ በቀረበው የድምፅ መስጫ ሊንክ በመግባት በየ24 ሰዓቱ ድምፅ በመስጠት እንድታበረታቷት ጥሪ ቀርቧል።
ዶክተር ፀዳለ ለገሰን ለመምረጥ እና ለስኬት እንድትበቃ ድጋፋችሁን ለመስጠት ከታች ያለውን የድረ ገፅ አድራሻ ይጠቀሙ። በየ24 ሰዓቱ ድምፅ መስጠት እንደሚቻል አይዘንጉ።
የድምፅ መስጫ ሊንክ፦
https://entrepreneurofimpact.org/2026/tsedale-legesse
#business #entrepreneurship #womenempowerment #innovation #ethiopianbusiness #successstory #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen









No comments yet.