“በኢትዮጵያ የነበረው የሚዲያ አፈና ተወግዶ ሰፊ የነጻነት ምህዳር ተፈጥሯል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዘርፉ …

- Advertisement -
Sidebar AD
“በኢትዮጵያ የነበረው የሚዲያ አፈና ተወግዶ ሰፊ የነጻነት ምህዳር ተፈጥሯል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
👉🏼 በዘርፉ ያሉ አንዳንድ አካላት ታስሮ እንደቆየ ጥጃ ነጻነቱን ማስተዳደር አልቻሉም ብለዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ” በኢትዮጵያ የነበረው የሚዲያ አፈና ተወግዶ ሰፊ የነጻነት ምህዳር መፈጠሩን ገለጹ። ሆኖም ይህ ነጻነት ከሙያዊ ሥነ-ምግባር እና ኃላፊነት ጋር ተጣጥሞ የመሄድ ክፍተት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ የለውጡን መንግሥት የመጀመሪያ እርምጃዎች የጠቀሱ ሲሆን፣ “የመጀመሪያው ሥራችን በሙያቸው ምክንያት የታሰሩ ጋዜጠኞችን መፍታት ነበር” ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ታግደው የነበሩ ብሎገሮች እና ድረ-ገጾች እንዲከፈቱ መደረጉን፣ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የሚዲያ ስርጭቶች ላይ ይደረግ የነበረው የጃሚንግ (የሞገድ እገዳ) ሥርዓት መቅረቱን፣ በስደት የነበሩ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ተቋማት ወደ ሀገር ቤት ገብተው እንዲሠሩ መፈቀዱን፣ እንዲሁም ለሚዲያ ነጻነት እንቅፋት የነበረው የፀረ-ሽብር ሕግ እንዲሻሻል መደረጉን ዘርዝረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚዲያው ዘርፍ የታየውን የሽግግር ወቅት በምሳሌ ሲያስረዱ፣ ሁኔታውን “ታስሮ እንደቆየ ጥጃ” በማለት ገልጸውታል።
“የታሰረ ጥጃ ሲፈታ ሁለት ባህሪያት ይታዩበታል፤ አንደኛው እንቅስቃሴ ስላልለመደ እግሩ እየተሳሰረ መቸገር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ያገኘውን ነጻነት በአግባቡ መቆጣጠር አቅቶት ዝም ብሎ በመዝለል ንብረት መስበር ነው” ብለዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በሚዲያው ዘርፍ የተሰማሩ አንዳንድ አካላት ነጻነቱን በአግባቡ የማስተዳደር እና የሙያ ሥነ-ምግባርን የመከተል ክፍተት እንደታየባቸው ጠቁመዋል።
ምንም እንኳን የሚዲያ አውዱ አሁንም ድረስ ከመረጃ አቅርቦት፣ ከገንዘብ እና ከተለያዩ ጫናዎች ጋር ተያይዞ እንከኖች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በመጨረሻም፣ ባለሙያዎች የተፈጠረውን የነጻነት ዕድል በመጠቀም ረገድ ራሳቸውን ሊፈትሹ እንደሚገባ አሳስበዋል።
“ሙያተኞች ሕግንና ሙያን እንዴት አጣጥመው እንደሚሠሩ ራሳቸውን መፈተሽ ይኖርባቸዋል” ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: