የሚዲያ ተቋማት ለእውነት መቆም እና ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር ይኖርባቸዋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሚዲያ ተቋማት እውነታን ለሕዝብ ይፋ በማድረግ ረገድ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸውና ለጋራ መግባባት መፈጠርም መስራት እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ በሚል መሪ ቃል በተካሄደውና በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶች ላይ በመከረው መድረክ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የሚዲያ ነፃነት ከሕጋዊ አሰራር ጋር ተጣጥሞ መሄድ እንዳለበት አሳስበዋል።

ቀደም ሲል የነበሩ አሳሪ ሕጎች በተለይም የፀረ ሽብር ሕጉ የመናገር ነፃነትን የሚገድቡ በመሆናቸው በለውጡ ማግስት እንዲሻሻሉ መደረጉን አስታውሰዋል።

በለውጥ ሂደቱ ወቅት የሚዲያ ምህዳሩን ክፍት በማድረግ ሁሉም የተለያየ አመለካከት ያለው አካል ሐሳቡን እንዲገልጽ ማድረግ ቀላል ተግባር እንዳልነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ የተሰጠውን ነፃነት በአግባቡ ማስተዳደር የተሳናቸው ሚዲያዎች መታየታቸውን ገልጸው፤ ነፃነትና ሕግን አቀናጅቶ መጓዝ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የሚዲያ ተቋማት በውይይት የሚያምኑ እና ለሀገራዊ ግቦች ስኬት ግንዛቤ ኖሯቸው የሚሰሩ መሆን እንደሚገባቸው አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈም ርዕሰ ጉዳይን በጥራት የመሸጥ አቅም ማነስ በኢትዮጵያ ሚዲያዎች ዘንድ እንደ አንድ ችግር የሚታይ መሆኑን አመልክተዋል።

#ሚዲያ #ነፃነት #ኢትዮጵያ #ውይይት #ሕግ
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: