የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ አክሱምን “ቅድስት ከተማ” ብሎ መሰየሙን እና ይህንኑ የሚያሳዩ “ሕጎችን

- Advertisement -
Sidebar AD

የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ አክሱምን “ቅድስት ከተማ” ብሎ መሰየሙን እና ይህንኑ የሚያሳዩ “ሕጎችን እያወጣ” መሆኑን አስታወቀ

#FastMereja I የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ ባደረገው ጉባኤ፤ የጥንታዊቷ አክሱም መጠሪያ “ቅድስት አክሱም ጽዮን ከተማ” እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ።

ቤተ ክርስቲያኗ፤ ይህንን ውሳኔ ተከትሎ በከተማዋ እንደ “መጠጥ እና ጫት” ሽያጭ ያሉ ተግባራት ላይ ክልከላ እንዲጣል እንደምትፈልግ እንዲሁም “የቅድስና ምልክት እንድታሳይ የሚያደርጉ ሕጎችን” እያወጣች መሆኑን ገልጻለች።

ውሳኔው ይፋ ከተደረገበት ሚያዝያ 28/2018 ዓ. ም. አንስቶ ከተማዋ በአጠቃላይ ቅድስት ተብላ እንደምትጠራ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አክሱም ከዚህ ቀደም ያላት ክብር እንዳለ ሆኖ በጠቅላላው ቅድስት ከተማ እንድትባል የሚያስችል ጥናት ቀርቦ ውሳኔው እንደተላለፈ ገልጸዋል።

አክሱም ከተማ “ቅድስት ከተማ” በሚል በተለምዶ ትጠራ እንደነበር ጠቅሰው የአሁኑ ውሳኔ መጠሪያውን “ሕጋዊ” እንደሚያደርገው አስረድተዋል።

አክሱም “ሕገ ልቦና፣ ሕገ ኦሪት፣ ሕገ ወንጌል ጠብቃ የኖረች የረዥም ዓመት የክርስትና ደሴት” ስለሆነች “ቅድስት” መሆኗን ብፁዕ አቡነ አረጋዊ አስረድተዋል።

“ብዙ መንበረ ታቦተ ጽዮናት፣ መንበረ ጽላት፣ መንበረ ሳምራ፣ መንበረ ብዙ ቅዱሳን ስለሆነች ያላት ክብር እንዳለ ሆኖ ከአሁን በኋላ ደግሞ ከተማዋን ጠቅላላ ቅድስት የሚያስብላት ተጠንቶ ያለው ግብዓት ቀርቧል” በማለትም አብራርተዋል።

“ከተማዋ በዚህ ዘመን ያላትን ቅድስና ቀጣዩ ትውልድ ይዞ እንዲሄድ” በሚል አጠቃላይ ከተማዋ ቅድስት ተብላ እንድትጠራ የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑን አክለዋል።

የትግራይ ጦርነትን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በተለዩት አባቶች የተመሠረተው የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክስርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ እንደተናገሩት፤ አክሱም በአጠቃላይ ቅድስት ከተማ እንድትባል በመወሰኑ ምክንያት መጠጥ እና ጫትን የመሳሰሉት ላይ ሙሉ በሙሉ ክልከላ ለመጣል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እያደረጉ ነው።

“ለሆቴሎችም ሥርዓት የሚወጣበት ሕግ እያወጣን ነው. . . ከተማይቷ ቅድስት ከተባለች የቅድስና ሥራ ሊሠራ ይገባል። ጠቅላላ ከተማዋ የቅድስና ምልክት እንድታሳይ የሚያደርጉ ሕጎች እያወጣን ነው” ብለዋል።

የከተማዋን “ጥንታዊ ታሪክ፣ ማንነቷን፣ ክብሯን ዓለም እንዲያውቀው” ማድረግም ዓላማቸው መሆኑን አክለዋል።

አሁን ላይ ከተማዋ “ለቅድስና የሚበቁ ነገሮች ማድረግ ስላለባት” ቤተ ክርስቲያኒቷን፣ ሕዝቧን እና ምዕመኗንም “በደንብ እንደሚያስተምሩ” ተናግረዋል።

ዘገባው የቢቢሰሲ አማርኛ ነው።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1