በሊጉ ዋንጫ ፉክክር ውስጥ ለመቆየትና ላለመውረድ የሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች የ36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በሊጉ ዋንጫ ፉክክር ውስጥ ለመቆየትና ላለመውረድ የሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች
የ36ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ አምስት ጨዋታዎች መደረግ ይጀምራል፡፡
ቀን 8 ሰዓት 30 ላይ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ ቼልሲን የሚያስተናግድበት መርሐ ግብር የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ነው፡፡
ሁለቱም ቡድኖች በአውሮፓ መድረክ የሚያሳትፋቸውን ውጤት ይዘው የውድድር ዓመቱን ለማጠናቀቅ እየተፋለሙ ይገኛል፡፡
በሊጉ ከሦስት ተከታታይ ድል በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ በማንቼስተር ዩናይትድ ሽንፈት ያስተናገደው ሊቨርፑል ወደ ድል ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
ያለፉትን ስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሊጉ የተሸነፈው ቼልሲ ወደ ድል ለመምጣት የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ቼልሲ በዛሬው ጨዋታ በሊቨርፑል የሚሸነፍ ከሆነ ከ74 ዓመታት በኋላ ሰባት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎችን የሚሸነፍ ይሆናል፡፡
አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከሰንደርላንድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን ያረጋገጠው ማንቼስተር ዩናይትድ በሊጉ አራተኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ይፋለማል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ፉልሃም ከቦርንማውዝ እንዲሁም ብራይተን ከወልቭስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ደጎሞ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ከብሬንትፎርድ የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በ35ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ነጥብ የጣለው ማንቼስተር ሲቲ የዋንጫ ፉክክሩን ለማስቀጠል ይፋለማል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ አርሰናል ነገ ምሽት ጨዋታውን እስከሚያደርግ ድረስ የነጥብ ልዩነቱን ወደ ሁለት ማጥበብ ይችላል፡፡
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: