የታዳጊዋ ማላኔ ኤረኖ ህልፈት አለፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ በከፋ የጤና እክልና በብቸኝነት ውስጥ ተገኝታ የብዙዎችን ቀልብ ስባ የነበረችው ታዳጊ ማላኔ ኤረኖ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፏ ተነገረ። በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የልጅቷን ህይወት ለመታደግ ሰፊ ርብርብ ቢያደርጉም፣ የህክምና ባለሙያዎች ጥረት ሳይሳካ ቀርቶ ታዳጊዋ ህይወቷ አልፏል።

​ታዳጊ ማላኔ ኤረኖ በመሎ ኮዛ ወረዳ በምትገኝ አንዲት ጠባብ ጎጆ ውስጥ ከሰው ተገልላ በከባድ ስቃይ ላይ እያለች ነበር መረጃው ለህዝብ ይፋ የሆነው። አቶ አለሙ አይሳ ባደረጉት ጥረት፣ ጉዳዩ የበርካታ ግለሰቦችና ድርጅቶችን ትኩረት ማግኘት ችሎ ነበር። ይህን ተከትሎም የተሻለ የህክምና እርዳታ እንድታገኝ ወደ ጣሊያን ሮም ተልካ አስፈላጊው ክትትል ሲደረግላት ቆይቷል።

​በሮም በነበረው የህክምና ሂደት ውስጥ ዶክተር ሰናይት ማርዮ እና ፕሮፈሰር አልዶ ሞሮኖ ግንባር ቀደም በመሆን ሙያዊ እገዛ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በገንዘብና በሞራል ከጎኗ አልተለዩም ነበር።

አሁን ከአቶ አለሙ አይሳ እንደሰማነው የታዳጊዋ ህይወት ማለጓፉን ነው። ለመላው ቤተሰቧ መጽናናትን እንመኛለን።





Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: