በካርግ ደሴት አቅራቢያ ከፍተኛ የነዳጅ ፍሳሽ መታየቱ ተገለጸ የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ኤክስፖርት ማዕከል በሆነችው የካርግ ደሴት …

- Advertisement -
Sidebar AD
በካርግ ደሴት አቅራቢያ ከፍተኛ የነዳጅ ፍሳሽ መታየቱ ተገለጸ
የኢራን ዋነኛ የነዳጅ ኤክስፖርት ማዕከል በሆነችው የካርግ ደሴት አቅራቢያ ከፍተኛ የነዳጅ ፍሳሽ መከሰቱን የሳተላይት ምስሎች አጋለጡ። እንደ ኮፐርኒከስ ባሉ የሳተላይት ክትትል ተቋማት የተለቀቁ ምስሎች በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በሚገኘው በዚህ ስትራቴጂካዊ የባህር ክልል ላይ ነዳጅ በስፋት ተሰራጭቶ ይታያል።
እንደ አለም አቀፍ የኢነርጂ ተንታኞች ገለጻ፣ ይህ የነዳጅ ፍሳሽ የተከሰተው አሜሪካ በኢራን ወደቦች እና በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የጣለችውን የባህር ላይ እገዳ ተከትሎ ነው። ኢራን የምታመርተውን ነዳጅ ወደ ውጪ መላክ ባለመቻሏ በደሴቲቱ ላይ የሚገኙ ግዙፍ ማከማቻዎች አቅማቸው መሙላቱንና ይህም ለቴክኒክ ብልሽትና ለፍሳሽ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
ኢራን 90 በመቶ የሚሆነውን የነዳጅ ምርቷን ለውጪ ገበያ የምታቀርበው በዚህ በካርግ ደሴት በኩል እንደመሆኑ መጠን፣ የተከሰተው ፍሳሽ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚፈጥር ተነግሯል።
በሌላ በኩል የኢራን ባለስልጣናት የፍሳሹን መኖር ቢያምኑም፣ መንስኤው ግን ከማከማቻ ታንከሮች ሳይሆን ከባህር ላይ መርከቦች የተለቀቀ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ ላይ ናቸው።
ከኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ ባለፈ፣ ይህ የነዳጅ ፍሳሽ በፋርስ ባህረ ሰላጤ ላይ ከፍተኛ የተፈጥሮ አካባቢ ብክለት ሊያስከትል እንደሚችል የስነ-ምህዳር ባለሙያዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
ሁኔታው በጣቢያው ላይ የሚገኙ የጥገና ባለሙያዎችን አቅም እየፈተነ ሲሆን፣ አሜሪካ በጣለችው እገዳ ምክንያት የጥገና ቁሳቁሶችን ለማስገባት መቸገሯንም መረጃዎች ያመለክታሉ።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: