ለ85 አማተር ከያንያን ለ10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የጽህፈተ ተውኔትና የትወና ስልጠና ተጠናቀቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአማራ ክልል ባህል ኪነ ጥበባትና ዝክረ ታሪክ ጽሕፈት ቤት እንዲሁም በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአገው ጥናት ኢንስቲቲዩት ትብብር የተዘጋጀው የኪነ ጥበብ ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።

ከ85 በላይ ሰልጣኞች የተሳተፉበት ይህ መርሃ ግብር ላለፉት አስር ቀናት በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ የመሰረታዊ ትወና እና የድራማ ድርሰት አፃፃፍ ትምህርት ሲሰጥ ቆይቷል።

የስልጠናው ማጠቃለያ ስነ ስርዓት በተለያዩ ጥበባዊ ስራዎች ደምቆ የቀረበ ሲሆን በተለይም በአርቲስት ንብረት ያለው ተፅፎ የተዘጋጀው አያና የፈንዞ ጌታ የተሰኘ ትውፊታዊ ቴአትር በሰልጣኞቹ አማካኝነት ለእይታ በቅቷል።

ከዚህም በተጨማሪ መዝሙሮች፣ መነባንቦችና ድራማዊ ህብረ ዝማሬዎች የቀረቡ ሲሆን ስልጠናው በከፍተኛ ድምቀትና በምረቃ ስነ ስርዓት ፍፃሜውን አግኝቷል።

#culture #arts #theatre #training #injibara #amhara #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: