ማንችስተር ሲቲ የሊጉን ዋንጫ የመውሰድ ተስፋውን ለማለምለም ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይፋለማል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ ለመቆየት የሚገደደው ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ከክሪስታል ፓላስ ጋር ወሳኝ ፍልሚያ ያደርጋል፡፡

ሲቲ ይህንን ተስተካካይ ጨዋታ በድል የሚወጣ ከሆነ ከመሪው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ ማድረግ ይችላል፡፡

አርሰናል በቅርቡ በዌስትሃም ላይ ያስመዘገበውን አስደሳች ድል ተከትሎ የሊጉን ዋንጫ የማንሳት ሰፊ እድል እንዳለው እየተነገረ ይገኛል፡፡

ማንችስተር ሲቲ ይህንን ግምት ውድቅ ለማድረግ ቀሪ የሊግ ጨዋታዎቹን በሙሉ ከማሸነፍ ባለፈ አርሰናል ነጥብ እንዲጥል ይፈልጋል፡፡

ይሁን እንጂ ዛሬ ማንችስተር ሲቲ ነጥብ አሳልፎ የሚሰጥ ከሆነ እና አርሰናል የፊታችን ሰኞ በርንሌይን የሚያሸንፍ ከሆነ መድፈኞቹ ከ22 ዓመታት በኋላ የሊግ አሸናፊ መሆናቸውን በይፋ ያረጋግጣሉ፡፡

ማንችስተር ሲቲ በቅርብ ዓመታት በክሪስታል ፓላስ ላይ የበላይነት ያለው ሲሆን በሁለቱ ክለቦች መካከል በተደረጉ የመጨረሻ ስምንት የሊግ ጨዋታዎች ሲቲ ሽንፈት አልገጠመውም፡፡ አምስት ጊዜ ሲያሸንፍ በሦስቱ አቻ ተለያይቷል፡፡

በዛሬው ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ሦስት ነጥብ ያገኛል ተብሎ ቢጠበቅም የመውረድ ስጋት የሌለበት ክሪስታል ፓላስ ያለ ጫና ስለሚጫወት ለሲቲ ከባድ ፈተና ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

በማንችስተር ሲቲ በኩል አማካዩ ሮድሪ በዛሬው ጨዋታ የመሰለፍ እድሉ አነስተኛ ነው፡፡ ስፔናዊው ተጫዋች ቅዳሜ ለሚደረገው የኤፍ ኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ይደርሳል ተብሎ ይታሰባል፡፡

በተቃራኒው በጉዳት ምክንያት የብሬንትፎርዱ ጨዋታ ያመለጠው ተከላካዩ አብዱከድር ኩሳኖቭ ወደ ሜዳ ይመለሳል፡፡

እንዲሁም በጥር ወር ክሪስታል ፓላስን ለቆ ሲቲን የተቀላቀለው ማርክ ገሂ የቀድሞ ክለቡን የሚገጥምበት ሌላው የጨዋታው ትኩረት ነው፡፡

በኢትሃድ ስታዲየም የሚካሄደው ይህ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ምሽት 4 ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

#manchestercity #crystalpalace #premierleague #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: