ዳኒ ኢንተርናሺናል ፊልሞች ላይ የተወነ ድንቅ ተዋናይ ነው ። ቀን ዘራፊ ፊልም ላይም በተዋናይነት ተሳትፏል ሙሉ ፊልሙን ቁጭ ብ

- Advertisement -
Sidebar AD

ዳኒ ኢንተርናሺናል ፊልሞች ላይ የተወነ ድንቅ ተዋናይ ነው ። ቀን ዘራፊ ፊልም ላይም በተዋናይነት ተሳትፏል ሙሉ ፊልሙን ቁጭ ብሎ አይቶ ለሰርተፍኬት ሽልማት ሲወጣ የናፈቀውን የብሄራዊ ቲያትር መድረክ ጎንበስ ብሎ ስሞ ሽልማቱን ተቀበለ ።

ፕሮግራሙ ሲያልቅ ውጪ ላይ ዳኒ ከአንድ ጥግ ትንፋሽ አጥሮት ነፍስ ዉጪ ነፍስ ግቢ ትግል ይዞ ታየ ሁሉም ሰው ተደናገጦ ምን እንደሆነ ተጠየቀ በተዘጋ ትንፋሹ ሰውን ላለመረበሽ ሲል ዘወትር የሚተነፍስበትን ኦክስጅን ነቅሎ እንደመጣ ተናገረ ፤ በጣም ተገረምኩ በስማም ብሞትም ልሙት የሚያስብል ምን አይነት የጥበብ ፍቅርና ክብር ነው ይሄ 🥺 ብቻ ከዛ ከትንፋሹ ጋር በሲቃ እየታገለ ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ተወስዶ ኦክስጅን ተሰክቶለት እዛው አደረ ።

አጋጣሚው ደነቀኝም እጅግ አስከፋኝም !!! እናላችሁ ዳኒ ረጅም አመት በኦክስጅን እየታገዘ ነው የሚተነፍሰው ነገር ግን የተወሰነ ትብብር ቢደረግና ቢታገዝ በህክምና መዳን የሚችል መሰለኝ ።

ዳኒዬ ያከበርካት ጥበብ በሰወች ተገልጣ እንደምትክስህ አምናለሁ 🙏 እባካችሁ ሼር በማድረግ ማገዝ ለሚችሉ ደጋጎች አድርሱልኝ አመሰግናለሁ 🙏

1000522370456
ዳንኤል ታደሰ /ንግድ ባንክ/

✍️ በረከት ወረደ ማያ


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2