60 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ወደ ራስ-ገዝነት ሽግግር እንዲገቡ ይደረጋል ተባለበኢትዮጵያ…

- Advertisement -
Sidebar AD
60 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ወደ ራስ-ገዝነት ሽግግር እንዲገቡ ይደረጋል ተባለ
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ታሪክ ከ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወደ ራስ-ገዝነት ለመሸጋገር ዝግጅት እያደረጉ ያሉ ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ህልውና በ60 በመቶ ውጤት ላይ የተንጠለጠለ መሆኑ ታውቋል።
በወጣው መመሪያ መሠረት፣ በትምህርት ሚኒስቴር የተዋቀረውና በፕሮፌሰሮች የሚመራው ገለልተኛ የግምገማ ቡድን ከዛሬ ግንቦት 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተቋማቱ የሚሰማራ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ካቀረቡት ሪፖርት ባለፈ በተጨባጭ ያላቸው ዝግጁነት ይፈተሻል።
የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ እንደገለጹት፣ ይህ ግምገማ ለተቋማቱ የ”መኖር ወይም አለመኖር” ያህል ወሳኝ ነው ብለዋል።
በገለልተኛ ቡድኑ በሚደረገው ጥብቅ ግምገማ 60 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት የሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ወደ ራስ-ገዝነት ሽግግር እንዲገቡ ይደረጋልም ተብሏል።
ይህንን ውጤት ማምጣት ያልቻሉ ተቋማት ግን የሽግግሩ ዕድል እንደሚያመልጣቸው ተጠቁሟል።
ለዚህ ፈታኝ ግምገማ የቀረቡት እነ መቀሌ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ጅማ፣ ሐዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ሐረማያ እንዲሁም የአዲስ አበባና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው። ከመጪው 2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን ለመረከብ እነዚህ ተቋማት የ60 በመቶውን መስፈርት ለማለፍ ትልቅ ፉክክር ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለአለም አሰፋ
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1