#Ethiopia | በህንድ በህዝብ ብዛቷ ቀዳሚ በሆነችው ኡታር ፕራዴሽ ግዛት የተከሰተ ከባድ ዝናብ እና በረዶ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ የ90 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ ተረጋግጧል።
የግዛቲቱ ባለስልጣናት ለሮይተርስ እንደገለጹት ከሆነ፣ የተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ በክልሉ ሰፊ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የንብረት ውድመት እና የሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል።
በአሁኑ ወቅት የአደጋው ሰለባ የሆኑ ወገኖችን ለመርዳት የነፍስ አድን ስራዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተከናወኑ ቢሆንም፣ የጉዳቱ መጠን ሰፊ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል።
አውሎ ንፋሱ በቤትና በመሠረተ ልማቶች ላይ ያደረሰው ውድመት በነፍስ አድን ስራው ላይ ተግዳሮት መፍጠሩም ተነግሯል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#India #UttarPradesh #DisasterNews #WeatherUpdate #IndiaNews #GlobalNews #GetuTemesgenMedia
Source: GetuTemesgen









No comments yet.