#Ethiopia | በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የቀበና ወንዝ ተፋሰስ በዘላቂነት ለማልማት የሚያስችል የ5 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግሥታት መካከል ተፈርሟል።
የቀበና ወንዝ ገባር ወንዞች ልማት ፕሮጀክት ተብሎ የተሰየመው ይህ ዕቅድ በአዲስ አበባ የውበትና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ አማካኝነት ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።
የልማቱ ዋነኛ ግብ የወንዙን ተፈጥሯዊ ስነ ምህዳር መልሶ በማደስ የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገጽታ መቀየር ሲሆን ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተበከሉ ሁለት ገባር ወንዞችን መልሶ ለማልማት ትኩረት ያደርጋል።
በሥራውም የፍሳሽ ማስወገጃ ግንባታዎችን ማከናወን፣ የጎርፍ መከላከያ ግንቦችን መገንባት፣ የወንዝ ዳርቻዎችን በዘመናዊ ጥበብ መጠበቅ እንዲሁም የአረንጓዴ መናፈሻዎችንና የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎችን ማቋቋም ይካተታሉ።
ይህም የወንዝ ብክለትንና የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባለፈ ለነዋሪዎች ጽዱና ለጤና ተስማሚ የሆነ የመዝናኛ ስፍራ እንደሚፈጥር ታምኖበታል።
#የቀበናወንዝ #አረንጓዴልማት #ኢትዮጵያናጣሊያን #የአየርንብረትለውጥ #አዲስአበባ #ልማት
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.