በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህ-ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀ ስጋ ተያዘ​በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህ-ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀ ስጋ ተያዘ

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በተካሄደው ድንገተኛ ኦፕሬሽን በድብቅ የታረደና ለገበያ ሊቀርብ የነበረ ከፍተኛ መጠን ያለው የእንስሳት ስጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተገለፀ።
 
​ኦፕሬሽኑ የተካሄደው በወረዳ 11 ልዩ ቦታው ቀጠና 01 “ሰው ለሰው እድር ቤት” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፣ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ ጤንነታቸው ያልተረጋገጡ 13 የታረዱ በጎች፣ 14 ፍየሎች እንዲሁም ፅዳቱ ያልተጠበቀ 312 ኪሎ ግራም ስጋ ተይዟል።
 
​የወረዳው የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሉ ምንዳ እንደገለጹት የተያዘው ስጋ እንዲወገድ ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተረከበ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸሙ ግለሰቦችም በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።
 
ኃላፊው አክለውም ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ እርዶችንም ሆነ ማንኛውንም የደንብ መተላለፍ ሲመለከት በነፃ ስልክ መስመር 9995 ጥቆማ በመስጠት ከተቋሙ ጎን እንዲቆም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
 

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: