ዶናልድ ትራምፕ በቤጂንግ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቤጂንግ ሲደርሱ በታላቁ የህዝብ አዳራሽ ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት ተደርጎላቸዋል።

ትራምፕ ከቻይናው መሪ ሺ ጂንፒንግ ጋር የሚያደርጉት ውይይት በዋነኝነት በንግድ፣ በቴክኖሎጂ ፉክክር፣ በታይዋን መጻኢ እድል እና በኢራን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኩራል ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከጉዟቸው አስቀድሞ ባስተላለፉት መልዕክት ቻይና የንግድ ገበያዋን ለአሜሪካ ኢንደስትሪዎች እና የግብርና ምርቶች ክፍት እንድታደርግ ፍላጎታቸውን ገልጸዋል።

በጉብኝታቸውም እንደ ቴስላ እና ኤንቪዲያ ያሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት መሪዎችን አስከትለዋል።

በሌላ በኩል የቤጂንግ ባለስልጣናት በአሜሪካ የሚጣሉ የታሪፍ ጫናዎች እንዲቀንሱ እና በታይዋን ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም ለማንጸባረቅ አቅደዋል።

ይህ የትራምፕ ጉብኝት በፈረንጆቹ 2017 ካደረጉት ጉዞ በኋላ ወደ ሥልጣን ተመልሰው ወደ ቻይና ያቀኑበት የመጀመሪያው አጋጣሚ ነው።

ቀደም ሲል በመጋቢት ወር ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ይህ መርሃ ግብር በኢራን ጦርነት ምክንያት ተራዝሞ አሁን በግንቦት ወር ሊከናወን ችሏል።

#DonaldTrump #China #USA #XiJinping #Beijing #TradeWar #InternationalNews
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: