የቢሊየነሮቹ የኤለን መስክ እና ሳም አልትማን ክስየቴክኖሎጂው ዓለም ግዙፍ ስሞች በሆኑት በኤለን መስክ እና በሳም አልትማን መካ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የቢሊየነሮቹ የኤለን መስክ እና ሳም አልትማን ክስ
የቴክኖሎጂው ዓለም ግዙፍ ስሞች በሆኑት በኤለን መስክ እና በሳም አልትማን መካከል የተጀመረው ታሪካዊ የሕግ ፍልሚያ ከፍተኛ ትኩረትን ስቧል።
ይህ የፍርድ ቤት ክርክር የቻት-ጂፒቲ ፈጣሪ የሆነውን የኦፕን-ኤአይ የወደፊት ዕጣ ፈንታ እና የሁለቱን መሪዎች ስምና ዝና የሚወስን ነው።
የኤለን መስክ ዋና ክስ አልትማን ‹‹ሰብአዊ ረድኤት ድርጅትን ዘርፏል ››የሚል ሲሆን፤ ኦፕን-ኤአይ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሆኖ ይቀጥላል በሚለው ቃል ኪዳኑ እያታለለ ነዉ ሲል ይሞግታል፡፡
ሳም አልትማን በበኩሉ ይህንን ክስ በፅኑ ያጣጥለዋል።
ባለፉት ሶስት ሳምንታት በካሊፎርኒያ የፌደራል ፍርድ ቤት የተካሄደው የሙግት ሂደት አስገራሚ የጽሑፍ መልዕክቶች እና ስልጣንን ለማግኘት ሲባል የቴስላ መኪናዎች በነጻ ስለመቅረባቸው የሚያሳዩ ሚስጥሮች የተጋለጡበት ነበር።
በችሎቱ ላይ የቀረቡ በርካታ ታዋቂ ምስክሮች ግን የኤለን መስክን ክስ አስተባብለዋል።
ከተደመጡት ምስክሮች መካከል የኦፕን-ኤአይ ተባባሪ መስራች ኢልያ ሱትስኬቨር፣ የቀድሞ የቦርድ አባል ታሻ ማኮሊ እና የማክሮሶፍት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳትያ ናደላ ይገኙበታል።
ናደላ ማይክሮሶፍት በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር መዋዕለ ነዋይ ከማፍሰሱ በፊት ጥብቅ ምርመራ ማድረጉን አረጋግጠዋል።
መስክ ማይክሮሶፍትን የአልትማን ሴራ አጋዥ ነው በሚል አብሮ ቢከስም፤ የችሎቱ ሂደት ግን የዓለማችን ባለጸጋ የሆኑትን የኤለን መስክን ክስ የሚያስተባብሉ በርካታ ድምጾች የተሰሙበት ሆኗል።
ሳራ ዮሐንስ
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: