#Ethiopia | የማንችስተር ሲቲ ከ18 ዓመት በታች ቡድን በታላቁ የኤፌ ካፕ (FA Youth Cup) የፍጻሜ ጨዋታ የከተማ ተቀናቃኙን ማንችስተር ዩናይትድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዘንድሮውን የውድድር ዓመት በድል አጠናቋል።
ይህ ስኬት ለሲቲ በታሪኩ 5ኛ የኤፌ ካፕ ወጣቶች ዋንጫው ሲሆን፣ ቡድኑ በሜዳው ላይ ባሳየው ድንቅ ብቃት ክለቡ ለተተኪ ተጫዋቾች የሚሰጠውን ትኩረት ዳግም አስመስክሯል።
የሁለቱን ክለቦች የወደፊት ኮከቦች ብቃት ለመታዘብም የዋናው ቡድን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እና የቀድሞው የዩናይትድ ኮከብ ማይክል ካሪክ በስታዲየም ተገኝተው ጨዋታውን ተከታትለዋል።
የማንችስተር ሰማያዊዎቹ የከተማውን ኩራት በወጣቶቻቸው አማካኝነት ማስጠበቅ የቻሉበት ይህ ድል፣ በቀጣይ ለዋናው ቡድን ተስፋ የሚጣሉባቸው ታዳጊዎች መፈለቃቸውን የሚያበስር ሆኖ አልፏል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ManchesterCity #FAYouthCup #ManchesterUnited #FootballNews #PepGuardiola #ManCityU18 #Champions
Source: GetuTemesgen









No comments yet.