በላሎ | BALAALOO

- Advertisement -
Sidebar AD

አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮ

#Ethiopia | ታዋቂው ድምፃዊ፣ የዜማና የግጥም ደራሲ ስንሻው ሙለታ አዲስ የሙዚቃ ስራውን ለታዳሚ ሊያደርስ መሆኑን አስታወቀ።

በሙዚቃው ዘርፍ ለበርካታ ዓመታት የቆየው ስንሻው ለራሱም ሆነ ለሌሎች አንጋፋ የሙያ አጋሮቹ ድንቅ ሥራዎችን በማበርከት ይታወቃል።

ከሥራዎቹ መካከልም በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ “ጅራ ጅራ” ግጥም፣ “የኩሌኮ” እና “አድዋ” ግጥምና ዜማዎች ተጠቃሽ ናቸው።

በተጨማሪም ለአንዷለም ጎሳ “ሚቹ ኡጋ”፣ ለጫላ ጨመዳ “ቃራባ ቃረኔ”፣ ለእስኪያስ መዘምር “ጀርጀሬ” እንዲሁም ለረመዳን ጭሜሳ “ሸንኮሬ” የተሰኙ ሥራዎችን ግጥምና ዜማ ሰጥቷል።

እነዚህ የኪነ ጥበብ ሥራዎች ሀገርን፣ ማንነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን የሚሰብኩ ናቸው።

በተለይም በስንሻው የተጻፉት የሀጫሉ ሁንዴሳ “ጅራ ጅራ” እና “ጉተኮ” የተሰኙ ሙዚቃዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ክፍል ከሃምሳ በላይ ተማሪዎች ለዲግሪና ለማስተርስ ማሟያ ጥናታዊ ጽሑፍ የሰሩባቸው ሲሆን ሥራዎቹም በኬኔዲ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ በታሪክ ተቀምጠዋል።

ስንሻው ከሙዚቃ ሥራው ጎን ለጎን በትምህርቱ የገፋ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ከሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት በማስተርስ እንዲሁም ከመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ በሰርቬይ ዲፕሎማ አግኝቷል።

“በላሎ” የተሰኘው አዲሱ የሙዚቃ ሥራው “ስሜት ሀሳብን ከበለጠ እውቀት ባሪያ ይሆናል!” የሚል ትልቅ መልዕክት ያዘለ ነው።

ሙዚቃው ከግለኝነት እና ከስሜታዊነት ይልቅ አንድነትን፣ ፍቅርንና እውነትን የሚያንፀባርቅ መሆኑ ተነግሯል።

ይህ በጉጉት የሚጠበቀው “የበላሎ” የሙዚቃ ቪዲዮ አርብ፣ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በስንሻው ሙለታ የግል ዩቲዩብ ቻናል ለተመልካች ይለቀቃል።

https://youtube.com/@sinishawmuleta?si=w5YOCfjU3WbxjX3D

#sinshawmuleta #balalo #ethiopianmusic #oromomusic #newmusicvideo #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1