ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ከጋና ወሰደች
#Ethiopia | በጋና እየተከናወነ በሚገኘው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በ400 ሜትር አገኘች
በጋና አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ ባለው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች የ400 ሜትር የፍጻሜ ውድድር የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በድል አግኝታለች።
በከፍተኛ ጉጉት በተጠበቀው በዚህ የሩጫ ውድድር ላይ አትሌት አልዩ ድንቅ የሆነ የፉክክር ብቃት በማሳየት አንደኛ በመሆን አጠናቃለች።
ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አትሌቷ ገና ከጅምሩ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆና የቀረበች ሲሆን በተለይም ውድድሩ ሊጠናቀቅ መቶ ሜትር ሲቀረው ባሳየችው አስገራሚ ፍጥነት ተቀናቃኞቿን በመቅደም የድሉ ባለቤት ሆናለች።
#አትሌቲክስ #አፍሪካሻምፒዮና #አልዩ #ኢትዮጵያ #ስፖርት #ወርቅሜዳሊያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.