“አሁን ባለው ዳታ መሰረት 10 ሚሊዮን ህዝብ በደም ግፊት ህይወቱን ያጣል። በኢትዮጵያ የግፊት ተጠቂዎች መጠን 17.3 በመቶ ጨምሯል” – ኮሌጁ
በኢትዮጵያ በግፊት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከሌሎች ገዳይ የበሽታ አይነቶች በበለጠ እየጨመረ በመሆኑን፣ በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች በፊት ከነበረት በ17.3% መጨምሯል ሲል የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ መግለጹን ቲቃህ ተረድቷል።
እንዲሁም፣ እ.ኤ.አ በ2014 በዓለም ላይ 22% የነበረው የደም ግፊት ተጠቂዎች አሁን ላይ ወደ 33% ከፍ በማለት የ11 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን አስረድቶ፣ የተጠቂዎች መጠን “እየቀነሰ ሳይሆን እየጨመረ ነው የመጣው” ብሏል።
“አሁን ባለው ዳታ መሰረት 10 ሚሊዮን ህዝብ በደም ግፊት ህይወቱን ያጣል። ግን ያ ሁሉ በደንብ ከታከመና ግፊቱን መቆጣጠር ከተቻለ ይሄ ሁሉ ሞት መቀነስ የምንችለው ነው” ሲልም ገልጿል።
በዓለም የጤና ድርጅት ጥናት መሰረት በዓለም ላይ በእያንዳንዷ ሰዓት 1,000 ሰዎች በግፊት ህይወታቸው እንዲሚያልፍ፣ አዋቂ ከሆኑ ከሦስት ሰዎች ውስጥ አንዱ የደም ግፊት እንዳለበት በመግለጽ፣ ነገር ግን “ከእነዚህ ውስጥ ግማሾቹ የግፊት በሽታ እንዳለባቸው አያውቁም” ብሏል።
በዓለም ጤና ድርጅት ጥናት መሰረት በዓለም ላይ ካለው ጠቅላላ 8 ቢሊዮን ህዝብ 1.4 ቢሊዮን የሚሆኑት የደም ግፊት አለባቸው። ከእነዚህ ውስጥ ግፊቱ እንዳለባቸው የሚያውቁት 800 ሚሊዮን ሲሆኑ፣ 600 ሚሊዮን ደግሞ በሽታው እንዳለባቸውም አያውቁም።
የደምግፊት እንዳለባቸው ከሚያውቁት 800 ሚሊዮን የዓለም ህዝቦች 160 ሚሊዮን የሚሆኑት አውቀውም ህክምና ማድረግ አይጀምሩም።
ከ800 ሚሊዮኖቹ መካከል 630 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ህክምና ቢጀምሩም ተከታትለው ግፊታቸውን የሚቆጣጠሩት 320 ሚሊዮን ብቻ ናቸው።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.