ኢራን ላቀረበችው የሰላም ዕቅድ አሜሪካ ባለ አምስት ነጥብ ምላሽ መስጠቷን የቴህራን መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።
ለወታደራዊ እና ደኅንነት ተቋማት ቅርብ የሆነው ፋርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፤ አሜሪካ ካስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ መካከል ቴህራን አንድ የኒውክሌር ተቋም ብቻ እንዲኖራት የሚጠይቀው ይገኝበታል።
የኢራን ጦርነት የሚቆመው ቅድመ ሁኔታዎች ተከብረው ድርድር ሲካሄድ መሆኑም ተመልክቷል።
ኢራን ለጦርነቱ ካሳ እንዲሰጣት ብትጠይቅም አሜሪካ ጥያቄውን አልተቀበለችም።
ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም ግንባሮች ጦርነትን ማቆም የኢራን ቅድመ ሁኔታ ነው።
በተጨማሪም ማዕቀቦች እንዲነሱ ቴህራን ያቀረበችውን ጥያቄ ዋሽንግተን አልተቀበለችም።
ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ሉዓላዊነቷ እንዲከበር መጠየቋም ተገልጿል።
የፓኪስታንየአገር ውስጥ ሚኒስትር ሞህሲን ናቂቭ በኢራን እና አሜሪካ መካከል የተቋረጠውን የሰላም ንግግር ለማስቀጠል ቴህራን ገብተዋል።










No comments yet.